ከለውጡ ወዲህ በሶማሌ ክልል ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸው ተመለከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከለውጡ በኋላ በሶማሌ ክልል የተገኘውን ሰላም ተከትሎ በመሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸው ተገለጸ፡፡
በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን የተመራ የክልሉ እና የፌደራል መንግሥት ልዑክ በሚኒሶታ እና አካባቢው ከሚገኙ የክልሉ ተወላጆች ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም÷ ከለውጡ በኋላ 63 ወረዳዎች እና ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው እና የውሃ ችግር ባለባቸው የገጠር አካባቢዎች ከ150 በላይ የውሃ ፕሮጀክቶች መሠራታቸው ተብራርቷል፡፡
እንዲሁም ስምንት ግድቦች ተገንብተዋል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
የሆስፒታሎች ቁጥርም ከዘጠኝ በአጭር ጊዜ ወደ 18 ከፍ ማለቱ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
በግብርናው ዘርፍ በተሰራው ስራም ከፍተኛ ስኬት መመዝገቡ ነው የተገለጸው፡፡
ባለሃብቶች በክልሉ በሪል ስቴት፣ በዱቄት ፋብሪካና ማቀነባበሪያ፣ በእንስሳት እርድ፣ በታሸገ ውሃ ፋብሪካ እንዲሁም በሆቴል ዘርፍ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም ክልሉን ጨምሮ በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ስላሉ ዳያስፖራው ኢንቨስት እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!