የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለ300 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ለ300 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፉን ለተማሪዎቹ አስረክበዋል፡፡
በዚህም ሚኒስቴሩ 3ሺህ 600 ደብተር ፣ 300 የተማሪዎች ቦርሳ ፣ 600 እስክርቢቶ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ በወረዳው 10 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ሰርቶ እንደሚያስረክብም መገለፁን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻን ጨምሮ የፌዴራል ፣ የክልልና የወረዳው የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።