Fana: At a Speed of Life!

በ2015 በጀት ዓመት ከተኪ ምርቶች 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት 1 ሺህ የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል÷በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል፡፡

በዚህም የማምረት አቅም በ2014 በጀት ዓመት ከነበረው 52 በመቶ ወደ 55 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቁመው÷ ይህም ለአምራች ዘርፍ ትልቅ እድገት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በአምራች ዘርፍ በተሰራ ስኬታማ ስራ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በዘርፉ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ሃይል እና የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡም ተጠቁሟል፡፡

ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሬን ከማቅረብ ጋር ተያይዞ 650 ሚሊየን ዶላር ለማቅረብ ታቅዶ 452 ሚሊየን ዶላር መቅረቡ ተገልጿል፡፡

በኤፍሬም ምትኩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.