Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እስካሁን በ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የመርሐ ግብሩን ዕቅድ ለማሳካት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መገኘቱን ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ ኤልያስ ከድር የተናገሩት፡፡

ቀደም ሲል በተከናወኑ የውሃ እና ተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራዎች ደርቆ የነበረው ሐረማያ ሐይቅ ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለስ ሕብረተሰቡ በይበልጥ በአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ እንዲነሳሳ ማገዙንም ጠቁመዋል፡፡

በሐረርጌ ዞኖች የተገኙ ተሞክሮዎችን ወደ ክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለማስፋት በትኩረት እየተሠራ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡

ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 5 ቢሊየን ችግኝ መዘጋጀቱን ጠቅሰው÷ ከዚህ ውስጥ 11 በመቶው አትክልትና ፍራፍሬ ነው ብለዋል፡፡

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም የአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ 17 ሚሊየን ሰዎችን በማሳተፍ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በስፋት መተከላቸውን ጠቅሰዋል።

ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች በአማካይ 88 ነጥብ 5 በመቶ መጽደቃቸውን ነው አቶ ኤልያስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በሲፈን መገርሳ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.