ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) የኢትዮጵያ ተወካይ ፍራይ ዚሙድዚ ጋር ተወይተዋል፡፡
በውይይቱ ሁለቱ ተቋማት በተለይም በግብርናው ዘርፍ በጋራ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን መሳብ በሚቻሉባቸው ስትራቴጂካዊ መንገዶች ላይ መምከራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡