በሶማሌ ክልል ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጠ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ለታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዱሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ሙስጠፌ÷ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ መሰረተ ልማቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ግብርን በአግባቡ መክፈልና መሰብሰብ መሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት 16 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቁመው÷ ገቢውን ስኬታማ ለማድረግ ዕውቅና ያገኙ ግብር ከፋዮች የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በሶማሌ ክልል በ2015 የበጀት ዓመት 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 9 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በ2016 በጀት ዓመት የታቀደው ገቢ በስኬት ለመሰብሰብ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡