Fana: At a Speed of Life!

በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይተገበራል- ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመግስትና የግል ትምህርት ቤቶች አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ይተገበራል፡፡

እንዲሁም በትግራይ ክልል በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ይተገበራል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስርዓተ ትምህርቱ ከሥራና የተግባር የትምህርት አይነቶች በስተቀር በሁሉም የቀለም ትምህርት ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበርም አስታውቀዋል፡፡

የሥራና የተግባር ትምህርቶች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚተገበሩ ጠቁመዋል፡፡

ለስርዓተ ትምህርቱ ውጤታማነት ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ መተግበር መጀመሩ ይታወቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.