ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 5
መስከረም16 እና 17 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ ኮማንድ ፖስቱ እየሠራ ነው።
የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መከልከላቸው ይታወቃል። ይሄም ጽንፈኛና ዘራፊ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ሊያደርሱት የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው።
መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀድ አስፈልጓል።
በመሆኑም የሚከተሉት ትእዛዛት እንዲፈጸሙ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ ያስታውቃል፦
1. እነዚህ መሰባሰቦች ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ የሚውሉ ናቸው።
2. የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው።
3. በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር ግዴታ ነው።
መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ