Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የካንሰር ሕክምና ማዕከሉን በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ሠየመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረር ህይወት ፋና ሁሉን አቀፍ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የገነባውን የካንስር ሕክምና መስጫ ማዕከል በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ሠይሟል።

የማዕከሉ ስያሜ በክቡር አርቲስት ዶ/ር አሊ ቢራ በተሰየመበት ወቅት የተገኙት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዳሉት፥ ማዕከሉ በአርቲስቱ ስም መሰየሙ አርቲስቱ ለሀገር ካበረከተው ስራ አንፃር ይገባዋል።

አሊ ቢራ እድሜ ልኩን ለህዝቦች እኩልነትና ነፃነት እንደታገለ ሁሉ የካንሰር ማዕከሉም ለህዝቡ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት የአርቲስቱ የቅርብ ጓደኛ አቶ መሀመድ አህመድ ጠቁመዋል፡፡

የካንሰር ህክምና ማዕከሉም የዶ/ር ዓሊ ቢራ ስም በመያዝ ጥራት ያለው አገልግሎት ለህዝቡ መስጠት እንዳለበትም በመድረኩ ተመላክቷል።

አሊ ቢራ ለሰው ልጆች ያለው ክብርና በጎነት ከሰው ልጆች አዕምሮ የማይጠፋ ነው ያሉት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጀማል ዩሱፍ (ዶ/ር) ናቸው።

ማዕከሉን በአርቲስቱ ስም የተሰየመው አሊ ቢራ በህይወት እያለ ከካንሰር ህመም ጋር ሲታገል በመቆየቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የአሊ ቢራ ካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል ስያሜ ይፋ በተደረገበት ወቅት የአርቲስቱ ቤተሰቦችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በምንያህል መለሰ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.