Fana: At a Speed of Life!

በተከታታይ 2 ዓመት ያስፈተንኳቸው ተማሪዎች በሙሉ የማለፊያ ነጥብ ያመጡት ለጥራት በተሰጠው ትኩረት ነው – የባህርዳር ስቴም ት/ቤት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2 ተከታታይ ዓመታት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ሁሉም ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ያመጡበት የባህርዳር ስቴም ትምህርት ቤት የስኬቱ ምንጭ ለትምህርት ጥራት ትኩረት መሰጠቱ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስቴም ማዕከል ዳይሬክተር ተስፋ ተገኘ (ዶ/ር) ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ውጤቱ ተማሪዎችን ለማብቃት የተሰራው ስራ ፍሬ ማፍራቱን ያሳየ ነው ብለዋል።

በዚህ ዓመት 40 ተማሪዎችን ያስፈተነው ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉንም ተማሪዎች ማሳለፍ ከቻሉ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው።

ተማሪዎቹ በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት አምጥተው ተመርጠው መግባታቸው፣ ትምህርቱ በዩኒቨርሲቲ መምህራን የሚሰጥ መሆኑ፣ የተሻለ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የተሻለ የትምህርት ሽፋን የሚያገኙ መሆናቸው ለተሻለ ውጤት እንዳበቃቸው ተናግረዋል።

ሆኖም እንደሀገር የመጣው ውጤት የትምህርት ስርዓታችን ያለበትን ደረጃ የሚያሳይ መሆኑንና ችግሩን ለመፍታት በጋራ መስራት እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

የተገኘው ዝቅተኛ ውጤት የሁሉንም የጋራ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን በማንሳትም ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት ማህበረሰቡ በጋራ መስራት አለበት ብለዋል።

የባህርዳር ስቴም ትምህርት ቤት ተማሪዎቹ ባመጡት ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሦስተኛ መውጣት የቻለ ነው።

በአፈወርቅ እያዩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.