በጋምቤላ ያለው የማዕድን ሀብት ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክት እየተሠራ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለው የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለምቶ ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ዘመናዊ አመራረት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ተባለ፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ዛሬ በጋምቤላ ክልል አኙዋክ ብሔረሰብ ዞን ዲማ ወረዳ ተገኝተው የኢትኖ ማይኒንግ ኩባንያ የሥራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት እንደተገለጸው÷ በጋምቤላ ክልል ያለው የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለምቶ ለኢኮኖሚው ዕድገት አስተዋጽዖ እንዲያበረክት ዘመናዊ አመራረት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው፡፡
የማዕድን ሀብቱን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ እንደ ሀገር ወደ ሚፈለገው ለውጥ መድረስ እንደሚቻልም ነው የተመለከተው፡፡