Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ ያከናወናቸውን ስራዎች አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ገለጻ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ገለጻ አድርጓል።

የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርአያ (ፕ/ር) ÷ ገለጻው ኮሚሽኑ ከምስረታው ጊዜ አንስቶ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎችን በዝርዝር ለማሳወቅ ያለመ ነው ብለዋል።

እስካሁንም አካታችነትን ለማረጋገጥ እስከወረዳ ድረስ በመውረድ ስልጠናዎች እና ውይይቶች መደረጋቸውንና በአንዳንድ ክልሎችም የተሳታፊ ልየታ መከናወኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ በልየታ ሒደቱ የጾታና የዕድሜ ስብጥር እንዲኖር እና የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ ከፍ እንዲል እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በምክክር ሒደቱ 43 ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ገልጸው ÷ ከሲቪክ ማህበራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋርም በትብበር እየሰራን ነው ብለዋል።

ምክክሩ የዳያስፖራ ማህበረሰቡንም እንደሚያካትት በማንሳት እስካሁን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ውይይት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በዚህም ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አብራርተዋል።

ከችግሮቹ መካከል በዋናነት የሰላምን ጉዳይ ያስቀደሙ ሲሆን ÷ ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማና ተደራሽ እንዲሆን ሰላም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲያዊ እና በሃብት ማሰባሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ዓመት ብቻ በገንዘብ ሚኒስቴር በተከፈተ ትረስት ፈንድ ከ10 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡

በዘመን በየነ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.