Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መቀሌ ቅርንጫፍ ወደ አገልግሎት ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መቀሌ ቅርንጫፍ ወደ ነበረ አቅሙ መመለሱ ተገለጸ፡፡

የቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሄዋን ሰመረ ቀደም ሲል ለ261 የጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓቶችን ተደራሽ በማድረግ ይሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከተወሰኑ አካባቢዎች በስተቀር ለሁሉም ጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓቶችን ተደራሽ እያደረግን ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

በ2015 የበጀት ዓመት በጤና ፕሮግራም 1 ነጥብ 6 ቢሊየን እንዲሁም በመደበኛ ግዥ 90 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ መድኃኒቶች፣ የሕክምና መሳሪያዎች እና መገልገያዎችን አሠራጭተናል ብለዋል፡፡

ቅርንጫፉ የትግራይ ክልል እንዲሁም አጎራባች በሆኑ የአማራ እና አፋር ክልል የሚገኙ ወገኖችን የሕክምና ግብዓቶችን ተደራሽ በማድረግ ቀድሞ ወደነበረ የስርጭት አቅሙ መመለሱን ነው ምክትል ስራ አስኪያጇ ያረጋገጡት፡፡

በቀጣይም በይበልጥ ስርጭቱን ለማሳለጥ የሚመለከታቸው አካላት ለቅርንጫፉ ሰራተኞች እገዛ እና ክትትል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.