Fana: At a Speed of Life!

ሰንሻይን ኢትዮጵያ በፋርማሲዩቲካል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰንሻይን ኢትዮጵያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ኢንቨስትመንት ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ::

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከሰንሻይን ኢትዮጵያ ውል ቴክስታይል ፒኤልሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ አክሊሉ በውይይቱ÷ ሰንሻይን በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ በጋርመንት ዘርፍ ተሰማርቶ በስራ እድል ፈጠራ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ውጤታማ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።

አክለውም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ መዋዕለንዋዩን ለማፍሰስ ያሳየውን ፍላጎት አድንቀው፤ በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.