Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ባለፈው ዓመት በአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ከተተከሉ ችግኞች 84 በመቶዎቹ መፅደቃቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፈው ዓመት በአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ 84 በመቶዎቹ መፅደቃቸውን አስታወቁ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ በአረንጓዴ ዐሻራ የተከላ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተከሉት ችግኞች እንዲፀድቁ በመላ ሀገሪቱ የመንከባከብ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል ብለዋል።
 
በአማካይ 84 በመቶ የሚሆኑት መፅደቃቸው ደግሞ ለመጭው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምንዘጋጅበት በዚህ ወቅት፣ ጥረታችን ፍሬ ማፍራቱን መገንዘባችን ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
 
በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ 4 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸው ይታወሳል።
 
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበርም ከ300 ሚሊየን በላይ ችግኞችን በዘመቻ በመላው ሀገሪቱ በመትከል በህንድ ተይዞ የነበረን ክብረወሰን መስበሯም አይዘነጋም።
 
በዘንድሮው ክረምት ደግሞ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መንግስት አቅድ ይዟል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም እየተደረገ ያለውን ዝግኝት ለመገምገም ሰሞኑን በተለያዩ ቦታዎች ላይ የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.