Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደና የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ለአካባቢው መረጋጋት የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ ነው፡፡

በየደረጃው ያለው አመራር ተደራጅቶ ወደ ስራ መግባትና የፀጥታ ሃይሉን በመደገፍ ለክልሉ ሰላም መምጣት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ በበኩላቸው እንደገለጹት÷ የሠራዊቱ ተልዕኮ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስከበርና ከውጭ ወራሪ ሃይል መጠበቅ እንዲሁም  የዜጎችን ሰላም ማረጋገጥ ነው፡፡

እንዲሁም ክልሎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥማቸው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባር በማስፈፀም ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ገበያ ተስፋ  ÷ የክልሉን ሰላም ወደነበረበት መመለስ አለብን ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል የምስራቅ ዕዝ 116ኛውን የሰራዊት ቀን “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሰራዊት”በሚል መሪ ሐሳብ እያከበረ እንደሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.