የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ያነሰ ዓላማ የለውም – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ያነሰ ዓላማ የለውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚጸና የድል ሠራዊት’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ እየተከበረ በሚገኘው 116ኛው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የመከላከያ ሠራዊት ዋነኛ ዓላማው ሰላምን ማጽናት እንደሆነ ጠቅሰው፥ መከላከያ ደሙን የሚያፈሰው፣ አጥንቱን የሚከሰክሰው፣ ህይወቱን የሚሰዋው ሰላምን ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ ያነሰ ዓላማ የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተደራጀው ለኢትዮጵያውያን፣ የሚመራው በኢትዮጵያውያን እና የሚሰራው ለኢትዮጵያ ነው ብለዋል።
‘ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ’ የተባለው ሀሳብ በግልጽ የሚገልጸው ተቋም እንደሆነም አንስተዋል።
ሰራዊቱ በሄደበት ሁሉ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ክልሎች በአፍሪካ በተሰማራበት ሀገር በሙሉ አርሶ አደር የሚያግዘው፣ ትምህርት ቤት የሚገነባው፣ የሰላም፣ የልማት፣ የአንድነትና የህብረት ምልክት ስለሆነ ነው ሲሉም ነው የገለጹት።
የሰላም ምልክት የሆነው መከላከያ የልማት ምልክት ሆኖ እንዲቀጥልም የአስተሳሰብ፣ የአደረጃጀትና የማድረግ አቅም ላይ ሪፎርም መካሄዱን አስታውሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ በማንም ሃይል ተሸንፋ እንደማታውቅና አሁንም እንደማትሸነፍ እንዲሁም ማንንም ሀገር ያልወረረችና አሁንም ማንንም እንደማትወርም ነው ያነሱት።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንደስሙ ሀገር የመከላከል ስራውን እንደሚሰራም አስረድተዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!