Fana: At a Speed of Life!

ለአጣዬ ሆስፒታል ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሒውማን ብርጂ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለአጣዬ ሆስፒታል ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዳሙ አንለይ (ዶ/ር) ÷ድጋፉ በተደጋጋሚ ውደመት የደረሰበትን የአጣዬ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎቱን በሚገባ እንዲሰጥ ያግዘዋል ብለዋል።

ድጋፉ የላቦራቶሪና የአልትራሳውንድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ከ50 በላይ የሕክምና ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም የሆስፒታሉን ችግር በመለየት ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

የአጣዬ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ወሰን አስፍው በበኩላቸው÷ የተደረገው ድጋፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥርና ሆስፒታሉ የተሻለ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችለው ገልጸዋል።

ሆስፒታሉ አሁንም የሕክምና ግብዓቶች አንደሚያስፈልጉት ጠቁመው÷ አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ ሒውማን ብርጂ የሆስፒታሉን ችግሩ ተረድቶ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደብረ ብርሀን  ዩንቨርሲቲ  የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ  ድጋፉን በማስተባበር፤አቤኔዜር ወንጌላዊት ቤተክርስትያን  ከሲዊዲን እስከ ወደብ  በማጓጓዝና   በማስተባበርና ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል

 

በሰላማዊት ሙሉነህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.