Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የእርሻና ምግብ የንግድ ትርዒት ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የእርሻና የምግብ የንግድ ትርዒት በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ።

የንግድ ትርዒቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሕዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን÷ ከ70 በላይ ከሀገር ውስጥና ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅና ከአፍሪካ የመጡ ኩባንያዎች እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል።

ትርዒቱ የንግድ ትስስርን ለመፍጠርና ዓለም አቀፍ አጋርነትን ለማፍራት ያስችላልም ተብሏ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ መስፍን አሰፋ÷ የንግድ ትርዒቱ አምራቾች የገበያ ትስስር እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በመዲናዋ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር እና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዙ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር ለማድረግም የጎላ ሚና እንዳለው አመልክተዋል።

መሰል ዝግጅቶች በሀገር ውስጥና በውጭ ኩባንያዎች መካከል የንግድ ትስስር ለመፍጠርና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ማታቸውንም ኢዜአ ዘግቧ፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.