በኢትዮጵያ የሚገኙ የሚሊተሪ አታሼ ማህበር አባላት ጎብኝት አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ የሚሊተሪ አታሼ ማህበር አባላት ዛሬ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል÷ጉብኝቱ ለፖሊስና ለሚሊተሪው የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ትልቅ እድልን ይፈጥራል ብለዋል።
የፌደራል ፖሊስም በሕዝብና በመንግስት የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ከተለያዩ ሀገራት ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ በፈረንጆቹ 2030 በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት መካከል አንዱ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ እውን ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የወታደራዊ አታሼ ማህበር ዲን ኮሎኔል አሪስትድ ሪስቶ÷ ማህበሩ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጋር በትብብር ለመስራት እና ድጋፍ ማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደተደረገ መግለጻቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡