አትሌት ጽጌ ዱጉማ በቤልግሬድ የ800 ሜትር ውድድር የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጽጌ ዱጉማ በቤልግሬድ የቤት ውስጥ የ800 ሜትር ውድድር የቦታውን ፈጣን ሰዓት እና ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች፡፡
አትሌት ጽጌ ርቀቱን በ1 ደቂቃ 59 ሰክንድ ከ66 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው የቦታውን ፈጣን ሰዓት እና ክብረወሰን በማሻሻል ያሸነፈችው፡፡
በዚህ ርቅት አትሌት ትግስት ግርማ 2 ደቂቃ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 2ኛ ደረጃ መያዟን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡