አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተለያዩ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ።
አምባሳደር ታዬ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ-ተሞን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በተመሳሳይም ከፖርቹጋል አቻቸው ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከፖርቹጋል ጋር በቱሪዝም፣ ትምህርት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተባብራ መስራት ትፈልጋለች ብለዋል።
የፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ በበኩላቸው ሀገራቸው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን እንደምትደግፍ ገልፀዋል።