Fana: At a Speed of Life!

የዮርዳኖስ ቱሪዝም ሚኒስትር ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዮርዳኖስ ቱሪዝም ሚኒስትር መክራም ሙስጠፋ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው አዲስ አበባ ሲገቡ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ ኢትዮጵያና ዮርዳኖስ በቱሪዝም ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ስምምነቶችን እንደሚፈጽሙ ተጠቁሟል፡፡

በተለይም በሃይማኖት ቱሪዝም እና ጤና ቱሪዝም ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ውይይቶችን ከተለያዩ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር እንደሚያደርጉ ተጠቅሷል፡፡

በቆይታቸው የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንደሚጎበኙም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.