Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ሠላም ለማስጠበቅና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል – ስንታየሁ ወ/ሚካኤል (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂ ሠላም ለማስጠበቅና የሴቶችን የኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ “የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በመድረኩ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የጥናትና ምርምር ሚኒስትር ዴዔታ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል (ዶ/ር)÷ የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ተጨባጭ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ጠቅሰው÷ የሴቶች እኩልነት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ችግሮችን ለመቅረፍ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ም/ፕሬዚዳንት መስከረም አበበ በበኩላቸው÷ የሴቶች ሊግ አደረጃጀትን በማጠናከር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አዘጋጅነት በተካሄደው መድረክ የማሕጸን ጫፍ ካንሰር የግንዛቤ ፈጠራና የምርመራ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በሙሉ ዋቅሹሜ

ፎቶ ፡ በጸሎት መንገሻና ሃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.