በጀርመን በርሊን ዓመታዊው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በርሊን በየዓመቱ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኤግዚቢሽን (ITB) ጀምሯል::
ኤግዚቢሽኑ በመላው ዓለም የሚገኙ ስመጥር የቱሪዝም ኩባንያዎች እና ሀገራት ያላቸውን መዳረሻ እና የቱሪዝም አገልግሎት የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው::
በኤግዚቢሽኑ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፥ ኢትዮጵያ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እያከናወነች ያለውን ተግባር እያስተዋወቁ ይገኛሉ።
በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ የምታከናውነውን የመዳረሻ ልማቶች እና የቱሪስት መስህቦች እያስተዋወቁ እንደሆነ ተገልጿል።
ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋርም በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል::
በዚህ ኤግዚብሽን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ የሀገር ውስጥ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው::