Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ ከዴንማርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ ሲንድብጀርግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በሁለትዮሽ ግንኙነትና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ ከዴንማርክ ጋር በሃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአቅም ግንባትና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

የዴንማርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላረስ ሎኬ ራስሙሰን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ እቅድ መያዛቸውንም አድንቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ሀገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያሏቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.