Fana: At a Speed of Life!

የጤና መረጃ ሥርዓትን በማዘመን የጤና አደጋ ስጋት ትንተና እና ምላሽ ላይ ማዋል ይገባል – ዶ/ር መቅደስ ዳባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም÷ በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ላቦራቶሪዎችን አሁናዊ የሥራ ሂደት፣ በምን ሁኔታ እንደሚገኙና የሥራ አፈጻጸማቸውን በሚመለከት ማብራሪያ ተደርጐላቸዋል።

በተቋሙ የሚሰሩ የምግብ ሳይንስና ሥነ-ምግብ ምርምር፣ ሀገር አቀፍ የላብራቶሪ አሁናዊ ደረጃ፣ ብሄራዊ የአደጋ ምላሽ ማስተባበሪያ እና የሀገራዊ የጤና መረጃ በሚመለከትም ገለጻ ተደርጓል፡፡

ዶክተር መቅደስ ዳባ በተቀናጀ መልኩ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን አድንቀው÷ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በዚህም አቅምን ወደ ላቀ ዲጂታላይዜሽን በማሳደግ የዜጎች ጤና ነክ መረጃዎችን ከብሄራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ይገባል ብለዋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ የሚኖረውን የጤና መረጃ አሰባሰብ እና ትንተናን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ያግዛል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል ለድንገተኛ የጤና አደጋ መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ላይ የጤና መረጃዎችን ዲጂታላይዝ ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.