እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤትና ስቱዲዮ ለመጠገን ርክክብ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የሥራ ርክክብ ተደረገ፡፡
የጥገና ሥራውን ለማከናወን የሚያስችለው ርክክብ የተደረገው በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት መካከል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ቅርሱ የነበረውን ዐሻራና ይዘት በመጠበቅ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን ተከትሎ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው አሳስበዋል፡፡
የጥገና ሥራውም በተቀመጠለት ጥራት እና የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲከናወን አስገንዝበው ጥገናው ሲጠናቀቅም ለሀገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡