አምባሳደር ታዬ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴ ከኒውዝላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊንስተን ፒተርስ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሀገራቱ መካከል ስለሚከናወኑ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ ትብብሮች መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በሰብዓዊ ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎች የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና የባለብዙ ወገን የጋራ ጥቅሞች ላይ መክረዋል፡፡