የፓኪስታን የሲያልኮት ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የስፖርት አልባሳት ለማምረት ስምምነት ፈረመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን የሲያልኮት ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት አልባሳት ለማምረት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃና አርአያሥላሴ እና የሲያልኮት ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አብዱል ጋፎር የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር፣ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሻሪፍ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለውን ቁርጠኝነት ማሳየቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።