በሐረሪ ክልል 43 ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል 43 ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክረምት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብር ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወየሳና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የአመራር አካላት አስጀምረዋል።
የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ረምዛያ አብዱልሃብ በወቅቱ አንደገለፁት÷ የዘንድሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ ሁሉም ገጠር ቀበሌና ከተማ አስተዳደር ውስጥ ይካሄዳል።
በመርሐ ግብሩ የከፍተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንዲሁም ከወጣቶች ማህበራት አደረጃጀትና ከማህበረሰቡ የተውጣጡ 43 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በጎ ፈቃደኞቹ በአረንጓዴ አሻራ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ በድጋፍ፣ በደም ልገሳ፣ በመንገድ ደህንነት፣ በትምህርትና ጤናን ጨምሮ በ13 የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች እንደሚሳተፉ አመላክተዋል።