Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለተመላሽ ወገኖችም ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ46 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር 86 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ከነጋድ ባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.