የመዲናዋ ነዋሪዎች በነገው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በነገው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በነቂስ በመውጣት አረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ ቀረበ፡፡
የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ “ውድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ነገ በአንድ ጀምበር በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚከናወነው ችግኝ ተከላ በመሳተፍ ተደማሪና ተጨማሪ ድል በጋራ እናስመዝግብ” ብለዋል፡፡
በነቂስ ወጥተን እንትከል፤ ለመጪው ትውልድ ዐሻራ እናስቀምጥ ሲሉም ጥሪ አቀርበዋል፡፡