Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ማበርከቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ጥሪ አካል የሆነ አረንጓዴ ዐሻራ የማኖር መርሐ-ግብር በክልሉ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ኦርዲን በኤረር ወረዳ ችግኝ ከተከሉ በኋላ በሰጡት መግለጫ÷ ስጋት ፈጥሮ የቆየውን የደን መራቆት ከመከላከል አንፃር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም 70 በመቶ ለምግብነት እንዲሁም 30 በመቶ ለደን የሚያገለግሉ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልጸው÷ ሀገራዊ ጥሪውን ተከትሎ በንቃት ችግኝ በመትከል እየተሳተፉ ለሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

#አረንጓዴዓሻራ
#600_ሚሊዮን_ችግኝ_በአንድ_ጀምበር
#የምትተክል_ሀገር፤ #የሚያፀና_ትውልድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.