አቶ አሕመድ ሺዴ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገብተዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ እና በእርሳቸው ለተመራው ልዑክ በጽህፈት ቤታቸው አቀባበል አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ያቀኑት የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ሲሆን ፥ የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የስራ ክፍሎችን መመልከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።