Fana: At a Speed of Life!

ከ85 ሚሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ማሻሻያ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ85 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የባቲ ከተማ ንጹህ የመጠጥ ውኃ ማሻሻያ ፕሮጀክት ለአገልግሎት በቃ፡፡

በፀሐይ ኃይል የሚሠራው ይህ ፕሮጀክት 5 ሺህ 750 ወገኖችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

በውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ እንዲሁም በባቲ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ትብብር መሠራቱም ተመላክቷል፡፡

እያንዳንዳቸው በሰከንድ አምሥት ሊትር ውኃ ማመንጨት የሚችሉ ሁለት ጥልቅ ጉድጓዶች ተቆፍሮለታል ተብሏል፡፡

በዚህም ቀደም ሲል በከተማው የነበረውን የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት መቅረፍ ተችሏል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.