Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የሚሳተፉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡና በመገንባት ላይ የሚገኙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

አመራሮቹ በጉብኝታቸው በአዲስ አበባ የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያዘምኑ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እንዲሁም የኑሮ ውድነትን የሚያቃልሉ ፕሮጀክቶችን እንደተመለከቱ ተናግረዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በፓርቲው መደበኛ ጉባዔ ላይ 1 ሺህ 700 በድምጽ የሚሳተፉ የፓርቲው አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እና የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

እንዲሁም ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እደሚታደሙ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.