Fana: At a Speed of Life!

የአገው ፈረሰኞች በዓል የታሪካችንና አብሮነታችን  መገለጫ ነው-  ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአገው ፈረሰኞች በዓል የታሪካችን፣ የአብሮነታችን ብሎም የባህላችን ተምሳሌት መገለጫ ነው ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ ገለፁ፡፡

ሚኒስትሯ  85ኛውን የአገው ፈረሰኞች ማህበር ምስረታ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸው÷ “የአገው ፈረሰኞች በዓል ፌስቲቫል ታሪካችንን፣ አብሮነታችንን፣ ባህላችንን አስተሳስሮ በማቆየት ለዘመናት የኖረ የማህበረሰባችን እሴት ነው” ሲሉ  አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ይህን እድሜ ጠገብ ባህል መጠበቅ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡

በዓሉ ሲከበርም ባህላዊ እሴቶችን በማዳበር፣ በመጠበቅና አብሮነትን ለዓለም በማሳየት ጭምር ሊሆን እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.