Fana: At a Speed of Life!

የኒውክሌር ምህንድስና ፕሮግራም ልማትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኒውክሌር ምህንድስና ፕሮግራም ልማትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

 

በጄኔቫና ኦስትሪያ የተባበሩት መንግሥታትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

አምባሳደር ፀጋአብ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለዘላቂ ልማት ጥቅም ላይ ለማዋል በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን ለአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ አመራሮች ማስረዳታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ እና የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶንግዚን ፌንግ ÷የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለልማት ስራዎች በተለይም የምግብ ደህንነትን ለማርጋገጥ እንዲሁም ግብርናን ለማዘመን ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

 

በተጨማሪም አምባሳደር ፀጋአብ በአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ የአፍሪካ ሃላፊ ዶ/ር ሚኬል ኤድዋርድ ጋር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኒውክሌር ምህንድስና ፕሮግራም ልማትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በኢትዮጵያ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ማድረግን በተመለከተ መክረዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.