Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ያሉ መልካም ዕድሎችን በመጠቀም የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለጹ።

ርዕሰ መሥተዳድሩ ይህን ያሉት በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችም የከተማውን ነዋሪ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ፀጋዎችን በማልማት ለሀገር ዕድገትና ለሕዝብ ተጠቃሚነት የሚበጁ ልማቶች ላይ ትኩረት ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው÷ ጠንካራ ፓርቲን መገንባት፣ የብሔራዊ ገዥ ትርክትን ማጠናከር እና ውጤታማ የሰላም ግንባታ ሥራ የቀጣይ አቅጣጫዎች መሆናቸውን ተቁመዋል፡፡

ኢኮኖሚዊ ልማትን ማፋጠን እንዲሁም ማኅበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልም ከአቅጣጫዎቹ መካከል መሆናቸውን አንስተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.