Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ በትምህርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ትብብር እንደሚቀጥል አረጋገጠች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፊንላንድ በትምህርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር እያከናወነቻቸው ያሉ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቃለች፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ ከፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፊንላንድ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች በጥራትና በፍትሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ የሄደችበት መንገድ በሞዴልነት እንደሚወሰድ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን እና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ በሪፎርሙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

አምባሳደሯ በበኩላቸው ሀገራቸው በትምህርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በርካታ ሥራዎችን በትብብር እያከናወነች እንደምትገኝ እና ይህንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም በመምህራን የዐቅም ግንባታ፣ ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በሌሎችም የትምህርት ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ፊንላንድ ቁርጠኛ መሆኗን አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.