የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባዔውን በሐዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ጉባዔው ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ፤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
የክልሉ መንግሥት ያለፉት ሥድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
ጉባዔው በቆይታው የተለያዩ ሹመቶችን፣ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በጥላሁን ይልማ እና ተመስገን ቡልቡሎ