Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን የድንበር ንግድ የጋራ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የስብሰባው ዓላማ ሀገራቱ የተፈራረሙት የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ለመገምገም መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ዴዔታ ያስሚን ውሃብረቢ ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱን በመተግበር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከርም የስብሰባው ዓላማ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ስምምነቱ የሀገራቱን ሕዝቦች በኢኮኖሚ እንደሚያስተሣሥር እና በድንበር አካባቢ ሠላምና መረጋጋትን በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ማለታቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ስብሰባው ኮንትሮባንድና ሕገ-ወጥ ንግድ የመሳሰሉ ችግሮችን ለመፍታትና የድንበር ንግድ ፕሮቶኮል ስምምነቱን ተግባራዊነት ለማጠናከር የጎላ ሚና እንደሚኖረውም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.