Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሕገ-ወጥ የማዕድናት ዝውውርን ለመከላከል እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕገ-ወጥ የማዕድናት ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በሁለት መንገዶች ሕገ-ወጥ የማዕድናት ዝውውር እንደሚስተዋል የቢሮው ምክትል ኃላፊ አበባ ጌታሁን ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

አንደኛው በሕጋዊ ፈቃድ ሽፋን ከአሠራር ውጭ የሚታዩ እንቅስቃሴዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ሌላው ፈቃድ ሳይኖራቸው ማዕድናትን ማዘዋወር ነው ብለዋል፡፡

በሁለቱም ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ቢሮው እስከ ታችኛው የመንግሥት መዋቅር ድረስ ግብረ-ኃይል አዋቅሮ ተገቢውን ክትትል እያደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በሕገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው የተገኙ አካላትን ለሕግ ማቅረባቸውን እና ይዘውት የተገኘውን ማዕድናት በመሸጥ ለመንግሥት ገቢ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ክልል ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ያደረገ የማዕድን ምዝበራን የመካለከል እና የመቆጣጠር ሥራ ትኩረት እንደተሰጠውም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም አሠራሩን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ለመሥራት ዕቅድ መያዙን ነው ያመላከቱት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.