Fana: At a Speed of Life!

ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለበለጠ ተጠቃሚነት በትጋት እንሠራለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እስከ አሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለበለጠ ተጠቃሚነት በትጋት መሥራትታችንን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው፤ ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም፤ ቀኑን ስናከብር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከሚያስችሉ ሥራዎች ምን ያህል አሳካን፣ ምን ያህል ሴቶችን ሕይዎት የቀየሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን፣ ምን ያህል ሴቶችን ተጠቃሚ አደረግን እንዲሁም ምን ያህል ቅድሚያ ለሚገባቸው ሴቶች ቅድሚያ መስጠታችንን በተግባር አረጋገጥን በማለት እና ለሌሎች ተደማሪ ድሎች ራሳችንን በማዘጋጀት ነው ብለዋል።

ከዚህ አንፃር ለከተማችን ሴቶች ተጠቃሚነት የሠራናቸው ሥራዎች ፍሬ አፍርተዋል ብለዋል ከንቲባዋ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ውጤቶች በቂ ስላልሆኑ የሴቶችን አቅም በይበልጥ እያጎለበትን፤ እስከ አሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለበለጠ ተጠቃሚነት በትጋት መሥራታችንን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.