Fana: At a Speed of Life!

5ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያዘጋጀው የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር እና 5ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

ከኢፍጣር ሥነ-ሥርዓቱ ቀደም ብሎ ‘ቁርዓን – የእውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በውድድሩም በሁለቱም ጾታዎች፣ ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከድሬዳዋ አሥተዳደር የተውጣጡ ተወዳዳሪዎችን ተሳትፈዋል፡፡

አሸናፊ የሚሆኑ ሁለት ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው የዘመናዊ መኪና ተሸላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

ለቀሪዎቹ ተወዳዳሪዎችም እንደየደረጃቸው የገንዘብ እና የሐጅ ጉዞ ሽልማቶች መዘጋጀቱ ተጠቅሷል፡፡

ከአዲስ አበባ እና አጎራባች ከተሞች የተውጣጡ የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ክፍል ተወካዮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሥነ-ሥርዓቱ ላይተገኝተዋል፡፡

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.