Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የአቪዬሽን የሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 974 ተማሪዎች አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ካሴ ይማም እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡

ከተመራቂዎች ውስጥ 43 የአውሮፕላን አብራሪዎች፣ 448 የበረራ መስተንግዶ፣ 184 የጥገና ዘርፍ ፣ 44 የሆቴል ኦፕሬሽን እና 255 የኮሜርሻል ዘርፍና ሙያተኞች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቻይና እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸው ነው የተመላከተው፡፡

በአንዱዓለም ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.