በአሲድ የተጠቃ 300 ሺህ ሄክታር መሬትን ለማከም ዝግጅት ተደርጓል – ሚኒስቴሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለዘንድሮው የመኸር እርሻ 300 ሺህ ሄክታር በአሲድ የተጠቃ መሬትን ለማከም ዝግጅት መደረጉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡
በሚኒስቴሩ የአፈር ሃብት ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊሬ አብዬ እንደተናገሩት÷ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአሲዳማ መሬት ሽፋን ከሚታረሰው መሬት 40 በመቶውን ይሸፍናል፡፡
ይህን ተከትሎም አሲዳማ የእርሻ መሬትን በኖራ ለማከም ከአርሶ አደሩ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሲዳማ መሬት ባለፉት ዓመታት እንዲታከም በመደረጉ ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን አቶ ሊሬ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
ዝናብ በስፋት በሚያገኙ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው አሲዳማ አፈር ምርትና ምርታማነት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝም ተመልክቷል፡፡
በጸጋዬ ንጉስ