Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ጥቅምን የሚተገብር ዜጋ መፍጠር ለሀገር ኅልውና ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሔራዊ ጥቅምን የሚረዳ እና የሚተገብር ዜጋ መፍጠር ለሀገር ኅልውና እና የግዛት አንድነት መከበር ወሳኝ መሆኑን ምሁራን አስገነዘቡ፡፡

ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት፣ የተረጋጋ ፖለቲካ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ሀገርን መገንባት ከብሔራዊ ጥቅሞች መከበር የሚገኙ መሆናቸውን በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ሪያድ ዳውድ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡

በሁሉም ዘርፍ የተያዙ ሀገራዊ ግቦች ፍሬ እንዲያፈሩ ዜጎች ከምንም በላይ ሀገራዊ ማንነታቸውን ሊያገዝፉ እንደሚገባም መክረዋል፡፡

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አሥተዳደርና ፖለቲካ ጉዳዮች መምህር ዮሃናን ዮካሞ በበኩላቸው፤ ብሔራዊ ጥቅምን ለይቶ መረዳት ከሁሉም ዜጎች እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች ብሔራዊ ጥቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ ሀገራዊ ተልዕኳቸውን መፈፀም እንዲችሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.