Fana: At a Speed of Life!

ከ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ9 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ አጸደ አይዛ እንደገለጹት÷ፈቃዱ የተሰጠው በግብርና፣ በአገልግሎት እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ለመሰማራት ጥያቄ ላቀረቡ ባለሃብቶች ነው፡፡

አሁን ላይ 90 ሺህ 575 ሄክታር መሬት ተለይቶ መቀመጡን ጠቁመው÷ የሚመጡ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ጥያቄዎች አዋጪነታቸው እየታየ እንደሚስተናገድ አስረድተዋል።

ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ሥራ ሲጀምሩ ከ33 ሺህ ለሚልቁ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡

በሌላ በኩል የተሰጣቸውን መሬት ሳያለሙ አጥረው ያስቀምጡና ላልተገባ ስራ ሲጠቀሙ የተገኙ 34 ባለሃብቶች ውላቸው መቋረጡን የገለጹት ሃላፊዋ÷ለ62 ባለሃብቶች ደግሞ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.